3ኛው ሀገር አቀፍ የባህልና ቱሪዝም ፌስቲቫልና ኤግዚቢሽን በአርባምንጭ ከተማ
 
የደቡብብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከአተትዮጵያ ብሔራዊ የባህል ማእከል ፣ ከጋሞጎፋ አስተዳደርን ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመተባበር ከሚያዝያ 25 እስከ 30/2010ዓ.ም ድረስ በሚቆይ « የባህል ቱሪዝም ሀብቶቻችን ለዘላቂ ልማትና ለአንድነታችን»  በሚል መሪቃል በጋሞጎፋ ዞን በውቢቷ አርባምኝጭ ከተማ በደመቀ  ሁኔታ ተዘጋጅቶ ለታዳሚው ይቀርባል ፡፡
 
ስለክልላችን በጥቂቱ
 
ክልሉ 42ዐ7 ሜትር ከፍታ ካለው የጋሞ ጐፋው ጉጌ ተራራ እስከ 376 ሜትር  ከባህር  ጠለል በላይ ከፍታ ያለው የደቡብ ኦሞው ጨልባና ቱርካና ኃይቅ አካባቢ ያለው ዝቅተኛ ቦታን ጨምሮ በርካታ የተለያየ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጥን የያዘ በሐሩር፣ በቆላ፣ ወይናደጋና ደጋ የአየር ንብረትን የተከፋፈለ ለእርሻ ከብት እርባታ ምቹ የሆነና በደንም የተሸፈነ ክልል ነው፡፡ የአዋሣ የአባያ፣ ጫሞ፣ጨው ባህርና ቱርካና የመሳሰሉ ኃይቆች ኦሞ፣ጐጀብና ብላቴ ወንዞች ባለቤት ነው፡፡ ከገናሌ-ዳዋ ከባሮ-አኮቦ፣ ከኦሞ-ግቤ፣ በአጠቃላይ 32% የሚደርሱ ተፋሰሶችንም ይጋራል፡፡ የአጆራ፣ሎጊታና ጋቺት ፏፏቴዎች የነጭ ሣር፣ኦሞ ማዜና የማጐና የጨበራ ጩጩራ ብሔራዊ ፓርኮች የሚገኙበትና ሌሎችም ተፈጥሮአዊ መስህባች ገፅታዎች የሚገኙበት ነው፡፡
በተፈጥሮ፤በባህልና በታሪክ ቅርሶችና መስህቦች ረገድም ክልሉ በርካታ እሴቶች አሉት፡፡ ከፍተኛ የፖልዮ አንትሮፖሎጂካል የአርኪዮሎጂ የምርምር ስፍራ የሆነው የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ ኪብሽ፣ ፈጀጀ ፣ወይጦ፣ የቦላና  የኮንሶ ጋርዱላ  ሳይቶች፣ የጢያ፤ የጨልባ ቱቲቲ፤ የቱቱፋላና የሳካሮ ሰዶ ትክል ድንጋዮች፣ የሞቼ ቦራጐና ሌሎች ዋሻዎች ፤ አብያተ ክርስቲያናት እና መስጂዶች ይገኙበታል፡፡ ዘመናትን ያስቆጠሩ ጥንታዊ ቅርሶች እና የብሔሮች ፤ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቱባ የባህላዊ እሴት ባለቤት ነው ፡፡ በአጠቃላይ ክልሉ በህዝቦች መቻቻል፤ መፈቃቀድ ፤ መከባበር ፤ በአብሮነት የመኖር መልካም ባህላዊ እሴቶች ላይ የተገነባ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሀገራችን በአለም አቀፍ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው ቅርሶች አኳያ አብላጫዎቹ በዚሁ ክልል የሚገኙ በመሆናቸው ክልልሉን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ያደርገዋል ፡፡
 
የፌስቲቫሉ አላማ
 
የዚህ ፌስቲቫል ዋና አላማ  የክልሉን ብሎም  የሀገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቱባ የባህል ሀብቶችንና  የቱሪስት መስህቦችን  በተደራጀ መንገድ በማስተዋወቅና በማበልጸግ የህብረተሰቡን  ተጠቃሚነት  ለማጎልበትና  የክልሉን መልካም ገጽታ  በሀገርና በአለም  አቀፍ ደረጃ አጉልቶ ከማሳየትም  ባሻገር  የክልሉን ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አብሮነት የሚያግዝ ዝግጅት ነው ፡፡
 
በፌስቲቫሉና ኤግዚቢሽኑ ተዘጋጅተው ለታዳሚው የሚቀርቡ ዝግጅቶች
 

 1. በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቱባ ባህላዊ እሴቶች ፤ ባህላዊ አጊያጊጦች፤ ባህላዊ አለባበሳቸው ፣ ባህላዊ ጭፈራቸው እና የመሳሰሉት በራሳቸው በብሄረሰቦቹ የሚቀርቡበትና የሚታዩበት ዝግጅት፣
 2. በብሔር ብሔረሰቦች የሚመረቱ ባህላዊ የእደጥበብ ውጤቶች ለኤግዚቢሽን የሚቀርብበት፤
 3. በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶች  በኤግዚቢሽኑ ለታዳሚዎች ለጉብኝት ይቀርባሉ፣
 4. በክልሉ የባህል አንባሳደር ባህላዊ ሙዚቃዎች የሚቀርብበት ዝግጅት፣
 5. ፕሮግራሙን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች በጥናት አቅራቢዎች የሚቀርብበት ዝግጅቶች፣
 6. የተላያዩ የእደጥበብ አምራች ማህበራት የሚያመርቷቸውን ምርቶች በኤግዚቢሽኑ የሚያቀርቡበት፣
 7. የክልሉ ባህላዊ አወቀቶች ፡ባህላዊ መድሀኒቶች በኤግዚቢሽኑ የሚቀርቡ ሲሆን እነዚህና ሌሎች ታይተው የማይጠገቡና የሚናፈቁ ዝግጅቶች ተሰናድተው በዝግጅቱ የሚቀርቡ ሆናል

 
የዝግጅቱ መልእክቶች

 • “የባህልና ቱሪዝም ሀብቶቻችን ለዘላቂ ልማትና ለአንድነታችን”!
 • በዓለም ልዩ የሚያደርጉንን የመከባበር፣መቻቻል፣ የአብሮነትና  የመደጋገፍ ዕሴቶቻችንን ጠብቀን ለትውልድ እናስተላልፋለን!
 • ቱባና እምቅ የባህልና የቱሪዝም ሀብቶቻችንን በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማስተዋወቅ የሀገራችንን ብሎም የክልላችንን ተጠቃሚነትና በጎ ገፅታ እንገንባ!
 • ባህላዊ እሴቶቻችንን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል!
 • የባህል እሴቶቻችን በማልማትና በማስተዋወቅ ለቱሪዝም አገልግሎት እናዉላቸዉ!
 • ባህላዊ ቅርሶቻችን በመጠበቅ፣ በማልማትና በመንከባከብ ለቀጣዩ ትዉልድ እናስተላልፍ!
 • የጋራ የባህል እሴቶቻችን የአንድነታችን መሰረት ናቸዉ!
 • የአብሮነት ባህላችን ለሰላማችን መሰረት ነው!

 
አዘጋጆች
 
በደቡብብ/ብ/ሕ/ክ/መ       በኢትዮጵያ ብሔራዊ     በጋሞጎፋ ዞን አስተዳደር          በአርባምኝጭ
ባህልና ቱሪዝም ቢሮ          ባህል ማእከል                                                                     ዩኒቨርስቲ