Message from The Office

የክልሉ ባህል፤ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የክልሉን ብሄሮች፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች የታሪክ፤የቋንቋ፤የቅርስ፤የስነ-ጥበብ፤ሌሎች ባህላዊ እሴቶችን እና ተፈጥሯዊ ሃብቶች እንዲጠኑ እንዲጠበቁና እንዲለሙ በማድረግና የቱሪስት አገልግሎት ተቋማትም አገልግሎት አሰጣጣቸው ጥራትና ብቃት ያለው በማድረግ ያሉንን ሀብቶች በሃገር ውስጥና በውጭ በማስተዋወቅ የዘርፉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን በማሳደግ ህዝባችንን ተጠቃሚ የማድረግ ተልዕኮን በመሰነቅ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡ከዚህም በተጨማሪ በስፖርቱ ዘርፍ የዜጎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴን የማድረግ መብቶችን በመንተራስ ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት ኖሮት በመኖሪያ ቦታዎች በትምህርት ቤቶችና በሌሎች አካባቢ ያሉትን የማዘውተሪያ ስፍራዎች ማጠናከርና ሌሎችን በመገንባት ዜጎች በመልካም ስነምግባር የአካልብቃት የተገነባ አካልና አይምሮ ኖሮአቸው አምራች ዜጎች እንዲሆኑ እንዲሁም  ለዚህ ወጣቱ ትውልድ የሚኖረውን ተሳትፎበማሳደግእንደብዝሃነታችንለባህላዊስፖርቶችናለሴቶችትኩረትመስጠትምይኖርብናል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሃገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተከተለች ያለው የለውጥ ጎዳና ከኛ አልፎ በመላው ዓለም ይሁንታን ያተረፈ ሲሆን አንዳንድ ይህን አዲስ ፖለቲካና የዲሞክራሲ ጎዳና ያልደገፉ ኃይሎች በአንዳንድ ቦታዎች ግጭቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ ለጊዜውም ቢሆን ህዝባችንን ችግር ውስጥ እያስገቡት ይገኛሉ፡፡
ይህ ደግሞ የሃገራችንንም ሆነ የክልላችንን መልካም ገጽታና ስም ከማጥፋቱም በላይ የሰዎችን በሰላምናበ ደስታ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርን ባህል እንዲቀንስ በማድረግ ከቱሪዝም ዘርፉ ልናገኝ የምንችለውን ገቢ ሊቀንስ እንደሚችል ሊታወቅ ይገባል፡፡የሃገራችንን ብሎም የክልላችንን ህዝቦች ሰላም ጠብቆ የተጀመረው ልማት እንዲቀጥል ለማድረግ እና ለውጡ ካስገኛቸው ፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትሩፋቶች መጠቀም እንድንችል ሁላችንም ለሰላማችን ዘብ መቆም ይኖርብናል፡፡እስከ አሁንም አልፎ አልፎ የተነሱ ግጭቶችን ባካበትናቸው የዘመናት ባህላዊ ግጭት አፈታት ስርዓት በመጠቀም የሃይማኖት አባቶች፤የአካባቢ ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች የበኩላቸውን እንዲወጡ በቢሮአችን በኩል ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን፡፡
በሃገራችን ከሚገኙ ብሔሮች ፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ውስጥ ከሰባ በመቶ በላይ ማለትም 56 የሚሆኑት በክልላችን የሚኖሩ በመሆናቸው ክልላችንን በባህል እሴቶቹ በግምባር ቀደምትነት እንድንታወቅ አድርጎናል፡፡ይህም ብቻ ሳይሆን ክልሉ በተፈጥሮ፤በባህልና በታሪክ ሀብቶቹ የታደለ ሲሆን በተለይ ሀገራችን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤የሳይንስና የባህል ድርጅት /UNESCO/ በቅርስነት ካስመዘገበቻቸው 12 ቅርሶች ውስጥ ክልላችን ሶስት ቋሚ ቅርሶችንና አንድ የማይዳሰስ ወካይ ቅርስ ማለትም የሲዳማብሄር ዘመን መለወጫ/ፍቼጫንባላላን/ በማስመዝገብ ቀዳሚውን ደረጃ እንድንይዝ አድርጎናል፡፡ 
በቱሪስት መዳረሻነትም በተለይ በባህል ሀብቶች እምቅ የሆነ ልዩ አለባበስ፤አጋጌጥ፤አመጋገብ፤የተለያዩ ታሪካዊ የመገልገያ ቁሳቁሶች በክልላችን የሚገኙ በመሆናቸውም በተሻለ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ሰባት ብሔራዊ ፓርኮች በክልላችን የሚገኙ ሲሆን አምስቱ ማለትም የማጎ፤የማዜ፤የጊቤ፤የሎካ አባያ እና በተለይ በአፍሪካ ትልቁ ዝሆን ሀብቶቹ የሚታወቀው የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርኮች በቢሮአችን የሚተዳደሩ ናቸው፡፡የክልላችን ህዝቦች በሀገራችን የሚነገሩ አራቱንም የቋንቋ ቤተሰቦች ማለትም የሴማቲክ፤የኩሸቲክ፤ኦሞቲክና የኒሎ ሳራ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚኖሩበት በመሆኑም ልዩ ያደርገናል፡፡
እስከ አሁንም ግን ካሉን የቱሪዝምና የባህል እምቅ ሀብቶች አንጻር ህዝባችን ከዘርፉ እምብዛም ተጠቃሚ መሆን ባለመቻሉ አሁንም ቢሆን ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባቸው አንዱ የተጎዱና በመጥፋት ላይ ያሉ ቋንቋዎችን የማጥናት የመሰነድና እንዲለሙ ማድረግ የተለየ ርብርብን ይፈልጋል፡፡ በብሄር ብሄረሰቦቻችን ውስጥ ያሉትን ዕሴቶችም አጥንቶ ለተተኪ ትውልድ የሚደርስበትንና የመጤ ባህል ብረዛ አዲሱን ትውልድ የመታደግ ስራ ይጠበቅብናል፡፡
የቱሪስቱ የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎታችንን በማዘመንና ደረጃውን በማሳደግ ዘርፉን ማጎልበት ይገባናል፡፡በስፖርትም ዘርፍ ጤናማና ንቁ የልማት ተሳታፊ ዜጋ ለመፍጠር ህዝባችንን ባሳተፈObjectives:
መልኩ ለተሸለ ውጤት መትጋት ይኖርብናል፡፡ለሁሉም ማለትም ለቱሪዝም ዘርፉም ሆነ ለባህሉ እንዲሁም ለስፖርቱ የህዝባችንን እኩል ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪዬን አስተላለፋለሁ፡፡
አመሰግናለሁ